የወቅቱን የሊጉ ኮከብ ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ይመራሉ።
አራት ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች በግብፅ መዲና ካይሮ የሚከናወነውን የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ይመራሉ። ጥቅምት ስምንት የሶማልያው ደኬዳሀ ከ ግብፁ ዛሜሌክ የሚያካሂዱት የካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የሁለተኛው የቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ አራት ኢንተርናሽናል ዳኞች ይመሩታል።
በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ዳኛ ኢንተርናሽናል ዳኛ ማኑሔ ወልደጻድቅ በዋና ዳኝነት፤ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞች ተመስገን ሳሙኤል እና አሸብር ታፈሰ ደግሞ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ኢንተርናሽናል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ በአራተኛ ዳኝነት ጨዋታውን የሚመሩት ሲሆን ጨዋታውም በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይካሄዳል።