በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ላይ ሦስት ኢትዮጵያውያን ዳኞች ይሳተፋሉ።

ከህዳር 6 እስከ 23 በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ላይ ሦስት ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች እንዲሳተፉ ተመርጠዋል። በነገው ዕለት በሚጀመረው ውድድር ላይ ሀገራችን ወክለው የሚሳተፉ ዳኞች ደግሞ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሲሳይ ራያ፣ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ እና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ሙስጠፋ መኪ ናቸው። በሀገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት የተሰጠውና በአበበ ቢቂላና በድሬዳዋ ስቴድዮም የሚካሄደው ይህ ውድድር በነገው ዕለት ሶማልያ እና ደቡብ ሱዳን በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀምር ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ ቀን ነገ ርዋንዳን በመግጠም ውድድሯን ትጀምራለች።


