የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አዲሱ ክለብ ታውቋል

የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አዲሱ ክለብ ታውቋል

በኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ለመሰልጠን የተቃረበው የላይቤርያው ክለብ ታውቋል


ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ወደ አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ የላይቤርያ ክለብ ለማምራት ከስምምነት እንደደረሱ መግለፃችን ይታወሳል፤ ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሰረትም አሰልጣኙ የሚያመሩበት ክለብ ‘Liberian International Shipping & Corporate Registry’ ‘Liscr’ የተባለ ክለብ መሆኑ አረጋግጣለች። ከተመሰረተ የ30 ዓመት ታሪክ ያለውና መቀመጫነቱ በዋና ከተማዋ ሞኖሮቭያ የሜትሮፖሊታን ግዛት ክልል ውስጥ በሚገኝ ጋርድነርስቪል ውስጥ የሆነው ክለቡ በአሁናዊ የላይቤርያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በዘጠኝ ጨዋታዎችም 17 ነጥቦችን ሰብስቧል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የላይቤርያውን ክለብ ለማሰልጠን ከመስማማታቸው በፊት የኬንያው ጎር ማህያን ለማሰልጠን በእጩነት ከተያዙ አሰልጣኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተው የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻም Shipping Boys ለማሰልጠን ተስማምተዋል።

ነገ ወደ ስፍራው የሚያቀኑት አሰልጣኙ ይህን ክለብ ለማሰልጠን ያበቃቸው በሀገር ውስጥ ያላቸው የማሰልጠን ልምድ እንዳለ ሆኖ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የነበራቸው ስኬት እንደሆነ ታውቋል።