ያለፉትን አንድ ዓመት ተኩል በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበረው አጥቂ ከክለቡ ለመለያየት መቃረቡን ሰምተናል።

ከወላይታ ድቻ የታዳጊ ቡድን ፍሬ በመሆን እስከ ዋናው ቡድን ድረስ በመጫወት ራሱን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማስተዋወቅ የቻለው እና ያለፉትን አንድ ዓመት ተኩል በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ ያደረገው አጥቂው ቢኒያም ፍቅሩ ከክለቡ ጋር ያለው ቆይታ ሊያበቃ መሆኑን ሰምተናል።
ምንም እንኳን ተጫዋቹ የስድስት ወር ቆይታ የሚቀረው ቢሆንም በሁለቱም አካላት ለመለያያት የተቃረቡ ሲሆን ተጫዋቹም ካሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ የክለቡን ካምፕ መልቀቁ ታውቋል።
በቀጣይ ቢኒያም ማረፊያው በሀገር ውስጥ ክለብ አልያም ወደ ውጭ ሀገር ወጥቶ ይጫወታል የሚለውን ተከታትለን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

