ያለፉትን ዓመታት በአርባምንጭ ከተማ ያሳለፈው ተከላካዩ መዳረሻው ክለብ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚሰለጥኑት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ወደ ዝውውሩ በመግባት ፍራኦል መንግሥቱ ፣ አንዋር ሙራድ እንዲሁም በከፍተኛ ሊጉ አማኑኤል ግዛቸው እና እሱባለው ሙሉጌታ ለማስፈረም ተስማምተው የአቤል ሀብታሙን እና የሌሎች ነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን ደግሞ ተከላካዩን አካሉ አቲሞን ለማስፈረም ተቃርበዋል።
ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ሊግ የተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ያሰለፈው አካሉ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ቆይታ አድርጎ አሁን ለሁለት ዓመት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ለመስማማት ችሏል።

