ደጉ ዱባሞ የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ሆነው ይቀጥላሉ

ደጉ ዱባሞ የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ሆነው ይቀጥላሉ

በኢትዮጵያ መድን እና በአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ መካከል ያለው ልዩነት ተፈቶ አሰልጣኙ እንደሚቀጥሉ እርግጥ ሆኗል

በቅርቡ ኢትዮጵያ መድን ለ2019 የውድድር ዘመን አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ይታወቃል። ሆኖም ትናንት ባቀረብነው ዘገባ በክለቡ እና በአሰልጣኙ መከከል ንፋስ ሳይገባ እንዳልቀረ የሚጠቁም አንድ መረጃ ወደ እናንተ አድርሰን ነበር።

አሁን ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ መሠረት በሁለቱም በኩል ያለው ልዩነት በውይይት ተፈቶ አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ በይፋ የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ለመሆን ፊርማቸውን ማኖራቸውን አውቀናል። በቀጣዮቹ ቀናትም አሰልጣኙ ቡድኑን ወደ ማጠናከር ሥራዎች እንደሚገቡ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማሉ።