አሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ ከሚዲያዎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት ምን አሉ?

አሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ በአሁኑ ሰዓት ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ እየሰጡ የሚገኝ ሲሆን በስፍራው ከሚገኙ ጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል አሠልጣኙ እና ቡድናቸው ከሚዲያዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦላቸው አሠልጣኙ ምላሽ ሰጥተዋል።
አሠልጣኙ በምላሻቸው ከሚዲያዎች ጋር ከሙያዊ ግንኙነት ውጪ ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ሲጠቁሙ ጥያቄውን ያቀረበው ጋዜጠኛው ከተፈቀደው የ15 ደቂቃ የልምምድ ቀጠሮ ለውጦች ሲደረጉ እንደነበረ አንስቶ አሠልጣኙ የተፈጠሩት ስህተቶች የእርሳቸው ኃላፊነት እንዳልሆነ እና በፌዴሬሽኑ በአስተዳደራዊ ችግሮች እየተፈጠሩ ያለው ነገር ላይ እሳቸው መጠየቅ እንደሌለባቸው ተናግረዋል። እርሳቸው ኃላፊነታቸው ቡድኑን ማሰልጠን ብቻ እንደሆነ ተናግረው ፌዴሬሽኑ የፊፋ እና ካፍን ህግ ተመርኩዞ የ15 ደቂቃዎችን ህግ ለመተግበር ደንብ እንዳወጣና የእሳቸው ውሳኔ እንዳልሆነ ገልፀው ውሳኔውን ፌዴሬሽኑን እንደወሰነ ተናግረዋል።
አሰልጣኙ በንግግራቸው “እኔ ሚዲያውን አልጠራሁም። ፌዴሬሽኑ ነው የቀጠራችሁ ፤ አስተዳደራዊ ችግሮች ናቸው እኔ ስራዬ ማሰልጠን ነው።” በማለት ከቀጠሮ ውጪ ስለተፈጠረው ስህተት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

