“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ወደ አፍሪካ ዋንጫው ማሳለፍ በስምምነታችን ውስጥ አለ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመስከረም ወር አጋማሽ ከሱዳን እና ከሴኔጋር ጋር ላለበት የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ በዛሬው ዕለት ስለ ዝግጅቱ እና ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም በቀጣይ በሚደረጉ የማጣሪያ ጨዋታዎች ዋናው አላማቸው ማሸነፍ መሆኑን ጠቅሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ወደ አፍሪካ ዋንጫው ማሳለፍ በስምምነታቸው ውስጥ እንደተካተተም አንስተዋል።

