ዘግይተውም ቢሆን ወደ በዝውውሩ በመግባት ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉት ዐፄዎቹ አማካዩን የግላቸው አድርገዋል።

ከሰዓታት በፊት ግብ ጠባቂ አብዩ ካሳየን ማስፈረም የቻሉት ፋሲል ከነማዎች አሁን የቡጣቃ ሸመናን ዝውውር አጠናቀዋል። ከአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እያሳየ ያደገው አማካዩ አሁን በእግር ኳስ ሕይወቱ ሁለተኛ ወደ ሆነው ክለብ ፋሲል ከነማን ለሁለት ዓመት ተቀላቅሏል።

