አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ወደ ሌላ ክለብ አቅንቷል

አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ወደ ሌላ ክለብ አቅንቷል

በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው የመስመር ተከላካይ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል

ከአርባምንጭ የተገኘው እና በመቀጠል በአዲስ አበባ ከተማ፣ በድሬደዋ ከተማ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ደግሞ ከመቐለ 70 እንድርታ ጋር በግሉ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ለአደማ ከተማ ለመጫወት ተስማምቷል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት አዳማዎች ፍፁም አለሙን፣ ቦና አሊን እና ይሁን እንደሻው በማስፈረም ስብስባቸው ያጠናከሩ ሲሆን አሁን ደግሞ ለሁለት ዓመት የቀኝ መስመር ተከላካዮን አሰጋኸኝ ጴጥሮስን የግላቸው በማድረግ አራተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።