ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለገቡን ተከላካይ አስፈረመ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለገቡን ተከላካይ አስፈረመ

በሸገር ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ኤሌክትሪክ አመራ

እስካሁን ባለው የዝውውር እንቅስቃሴያቸው ፍራኦል መንግስቱ ፣ አንዋር ሙራድ እንዲሁም አማኑኤል ግዛቸው እና እሱባለው ሙሉጌታን አስፈርመው አቤል ሀብታሙን ጨምሮ የአራት ተጫዋቾ በቡድኑ ማቆየት የቻሉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን ደግሞ አቤል አየለ ለማስፈረም ተስማምተዋል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ወጥቶ በለገጣፎ ለገዳዲ እና ሸገር ከተማ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ወደ ኢትዬ ኤሌክትሪክ ለማቅናት ተስማምቶ በቅርቡ ፌርማውን ያኖራል።