አዲስ አዳጊዎቹ የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል ማራዘም ችለዋል።

በአዲሱ የውድድር ዓመት ቡድናቸውን ለማጠናከር
ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማሳደግ የቻሉ የነባር ተጫዋቾችን ውል አራዝመው ኮንኮኒ ሀፍዝ ፣ ካሌብ አማንክዋህ እና ሴኔጋላዊ የተከላካይ አማካይ ሳምባ ሴክ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ሀላባ ከነማዎች የፀጋ ከድር ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።
በሀላባ እግር ኳስ ጅምሮ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ካሳለፈ በኋላ በኢትዮ ኤሌትሪክ እና በደሴ ከተማ ቆይታ አዳርጎ ወደ ትውልድ ሀገሩ ሀላባ በመምጣት ቡድኑ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲያድግ የበኩሉን ያበረከተው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት በቡደኑ ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል።

