ሶፎንያስ ሰይፈ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቅንቷል

ሶፎንያስ ሰይፈ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቅንቷል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምዓም አናብስቱ ቆይታ የነበረው ግብጠባቂ አስፈረመ

ላለፉት ሁለት ዓመታት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ያሳለፈው ግብ ጠባቂው ሶፎንያስ ሰይፈ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምርቷል። ከደደቢት ሁለተኛ ቡድን የተገኘው እና በአሳዳጊው ክለብ ጨምሮ ከዚህ ቀደም በመቐለ 70 እንደርታ ፣ ንብ እና ገላን ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲገባ እንዲሁምየፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ስያሳካ ጥሩ ግልጋሎት የሰጠበትን መቐለ 70 እንደርታ ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምርቷል።