ፈረሰኞቹ ከአማካያቸው ጋር ተለያይተዋል

ፈረሰኞቹ ከአማካያቸው ጋር ተለያይተዋል

ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ ያደረገው አማካይ ከቡድኑ ጋር ተለያይቷል።

በወቅታዊ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከአጥቂዎቹ ቢኒያም ፍቅሩ እና አቤል ያለው ጋር ከተለያዩ በኋላ በትናንትናው ዕለት ደግሞ ከአማካዩ አፈወርቅ ኃይሉ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።

ከዚህ ቀደም በድሬ ፖሊስ ፣ ወልዋሎ፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ባህር ዳር ከተማ እንዲሁም ዋናው እና የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድንን ማገልገል የቻለው አማካዩ ላለፉት አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ሲጫወትበት ከነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በዘንድሮው የውድድር ዓመት በስምንት ጨዋታዎች 353 ደቂቃዎችን ሜዳ ላይ ከቆየ በኋላ ከቡድኑ ጋር በስምምነት መለያየቱን አረጋግጠናል።