አቤል ያለው በይፋ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል

አቤል ያለው በይፋ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል

በቅርቡ ከፈረሰኞቹ ጋር የተለያየው አቤል ያለው ለሊጉ መሪ ፊርማውን አኑሯል።

የቀድሞ አቃቂ ቃሊት ፣ ደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም በግብፁ ዜድ ክለብ ቆይታ የነበረው አቤል ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመልቀቅ ከቀናት በፊት ያስገባው ደብዳቤ ምላሽ አግኝቶ በይፋ ቡድኑን መለያየቱ መዘገባችን ይታወቃል።

አቤልን ለማስፈረም በአሁኑ ሰዓት በይበልጥ ሁለት የሊጉ ክለቦች ጥረት እያደረጉ መሰማቱን እንዲሁ በነገርናችሁ መሠረት ሲዳማ ቡና አቤልን በይፋ ማስፈረሙ እርግጥ ሆኗል።

ዘንድሮ 15 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ 8 ጎሎችን ለክለቡ ያስቆጠረ ሲሆን የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ከአዲስ ግዳይ እና ታምራት ኢያሱ ጋር በጋራ እየመራ ይገኛል።