በነገው ጨዋታ ዙሪያ አዲስ ነገር ተሰምቷል

በነገው ጨዋታ ዙሪያ አዲስ ነገር ተሰምቷል

በብሔራዊ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ዙሪያ አዲስ ነገር ሊኖር እንደሚችል ተሰምቷል

ወደ ሞሮኮ አቅንተው ኤል-አብዲ ስታዲየም ላይ ከነአን ማርክነህ እና አቤል ያለው (2) ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 3-0 በማሸነፍ ወሳኝ ድል የተቀዳጁት ዋልያዎቹ የመልሱን ጨዋታ ነገ ማክሰኞ መጋቢት 22 በድሬደዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም እንደሚያደርጉ ይታወቃል።

ታዲያ ብሔራዊ ቡድናችን ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሩ ተመልሶ የሚያደርገው የመጀመሪያ ጨዋታ በዝግ ያለ ተመልካች እንዲያደርግ በካፍ ፍቃድ ማግኘቱ የሚታወስ ቢሆንም አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ጨዋታው ለተመልካች ክፍት የሚሆንበት ዕድል እንዳለ ሰምተናል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በዚህ ዙርያ ከሚመለከታቸው የካፍ አካላት ጋር እየተነጋገረ ሲሆን ጥረቱ የሚሳካ ከሆነም የነገው ጨዋታ የስፖርት ቤተሰቡ በስታዲየም ተገኝቶ የናፈቀውን የብሔራዊ ቡደን ጨዋታ የሚከታተል ይሆናል።