ቢጫዎቹ የመሀል ተከላካዩን ኪም ላም ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ እየተመሩ የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ወልዋሎዎች ስብስባቸውን ለማጠናከር እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ በመቀጠል የመሀል ተከላካዩ ኪም ላም ሉል ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።
በተጠናቀቀው ዓመት ሸገር ከተማን ለቆ ወደ ወልዋሎ በማምራት በክለቡ የአንድ ዓመት ቆይታ የነበረው ተከላካዩ ከመቻል ወጣት ቡድን ከወጣ በኋላ ባለፉት ዓመታት በባቱ ከተማ፣ ንብ እንዲሁም ሸገር ከተማ መጫወት ችሏል።
በዛሬው ዕለት የተከላካዩን ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ወልዋሎዎች በቀጣይ ቀናት ከዚህ ቀደም በክለቡ ለማቆየት እና ክለቡን ለመቀላቀል የተስማሟቸውን ተጫዋቾች ውል ለማፅደቅ እንዲሁም የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ምዘገባ ለማጠናቀቅ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ከክለቡ አረጋግጠናል።

