የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ፎርፌ አግኝቷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ፎርፌ አግኝቷል

ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏ ተረጋግጧል

ከሳምንታት በፊት በ 2027 የ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚ የሆነችው ዩጋንዳ ከማጣሪያ ውድድሩ ራስዋን ለማግለል መወሰኗ ይታወቃል።

ከአንድ ወር በፊት ነሐሴ 13 በወጣው ድልድል መሰረትም የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ማለትም መስከረም 18 እንዲካሄዱ መርሐ ግብር እንደወጣላቸው የሚታወስ ሲሆን ጨዋታው በዛሬው ዕለት አለመካሄዱ ተከትሎም የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት ብሔራዊ በፎርፌ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉ እርግጥ ሆኗል።

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ዙር ከሞሮኮ አቻው ጋር የሚጫወት ሲሆን የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያው ጨዋታ ጥቅምት 30 የመልስ ጨዋታ ደግሞ ሕዳር 8 ይካሄዳል። ይህ የማጣሪያ ውድድር በድምሩ 42 ብሔራዊ ቡድኖች የሚሳተፉበት ሲሆን ሦስቱ የማጣሪያ ዙሮችን ያለፉ ሰባት ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም አዘጋጅዋ ግብፅ በድምሩ ስምንት ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫው የሚሳተፉበት ይሆናል።