የሞዛምቢክ አሰልጣኝ ቺኵንሆ ኮንዴ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ምን አሉ?

የሞዛምቢክ አሰልጣኝ ቺኵንሆ ኮንዴ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ምን አሉ?

👉 “እንደ እውነቱ ከሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚገኝ ቡድን ነው”

👉 “ከእነዚህ ሁለት ጨዋታዎች ስድስት ነጥቦች….”

👉 “ቡድኑ ቀጥተኛ፣ ፈጣን እና በተናጠል ፍልሚያዎች በጣም ጠንካራ የሆኑ ተጫዋቾች አሉት”

ዩጋንዳ፣ ኬንያ እና ታንዛንያ በጣምራ ለሚያዘጋጁት የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገው ፍልሚያ ሦስተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ደርሷል። ከሞዛምቢክ፣ ሴኔጋል እና ሱዳን ጋር በምድብ ‘J’ የተደለደሉት ዋልያዎቹም በምድብ ማጣሪያው የመጀመሪያ ድል ፍለጋ ወደ ማፑቶ ያመሩ ሲሆን ቀደም ብለን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እና የቡድኑ አምበል ጋቶች ፓኖም በስፍራው ለሚገኙ የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኀን የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ማቅረባችን ይታወሳል። የሞዛምቢኩ ዋና አሰልጣኝ ፍራንሲስኮ ኲሪዮል ኮንዴ ጁንየር በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ያነሷቸው ነጥቦችም እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

የቴክኒክ ቡድናችን እና ተንታኞቻችን ከዚህ በፊት የተጫወቱትን በርከት ያሉ ጨዋታዎች ለመመልከት ሞክረዋል። ከተመለከትነው በተጨማሪም ከዚህ ቡድን ጋር በቻን ውድድር የመጫወት እድል ነበረን፤ እንደ እውነቱ ከሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚገኝ ቡድን ነው። በግልፅ ነገ ፉክክሩ ቀላል አይሆንም ሆኖም በዓላማችን በማመን ጨዋታውን ቀላል ማድረግ አለብን።

ስለ ጨዋታው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጣም ፈጣን አጥቂዎች አሉት። ቡድኑ ቀጥተኛ፣ ፈጣን እና በተናጠል ፍልሚያዎች በጣም ጠንካራ የሆኑ ተጫዋቾች አሉት። ተጫዋቾቻችንም ይህንን በሚገባ ያውቃሉ።

ጄን ለጨዋታው ደርሶልናል ጤናማ ነው፣ እንደ ሌሎች ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት እና በጥሩ ሁኔታ ዝግጁ ሆኗል። በትናንትናው ልምምድ ኤድ ሚልሰን መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል ነገር ግን በእርግጠኝነት ይደርሳል ብለን እናስባለን። በነገው ጨዋታ ጊማ ፣ ጊልዶ እና ባንጋል የሉም፤ ነገር ግን ራቲፎ ወደ ስብስቡ ተመልሷል በተጨማሪም እንደ ኦስቫልዶ፣ ክሪሚልዶ ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾች በቡድናችን ውስጥ ይገኛሉ።

ስለ ማጣሪያ ውድድሩ

ከሴኔጋል ከዚያ በኋላም ከሱዳን ጋር ተጫውተናል አራት ነጥቦችም አሉን። በግልፅ ለማየት እንደሚቻለው ቡድናችን በመንፈስ ደረጃ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው ጥሩ ተነሳሽነት አለን ከእነዚህ ሁለት ጨዋታዎች ስድስት ነጥቦች ማግኘት ለዓላማችን ወሳኝ እንደሆኑ በሚገባ ተገንዝበናል። ህዝብ በነቂስ ወጥቶ እንደ 12ኛ ተጫዋች እንደሚደግፈን ተስፋ አደርጋለሁ። ይህም የምናስበው ውጤት እንድናገኝ ይረዳናል።