👉“ከረጅም ጊዜ በኋላ በደጋፊያችን ፊት መጫወታችን ለኛ ትልቅ ስንቅ እና ሞራል እንጂ ጫና አይሆንብንም”
👉 “በመጀመሪያው ጨዋታ የታዩብንን ጥቃቅን ክፍተቶች አርመን በማሸነፍ ስሜት ወደ ሜዳ እንገባለን”

ዋሊያዎቹ ከዓመታት ቆይታ በኋላ በደጋፊዎቻቸው ፊት ወደ ሜዳ በሚመለሱበት የነገው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፍልሚያ ላይ የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት እና የቡድኑን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የቡድኑ አምበል ያሬድ ባየህ በቅድመ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሰጠውን ማብራሪያ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።
በተመለከተ የቡድኑ አምበል ሲያብራራ፤ ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ድረስ ባደረጋቸው በርካታ ጨዋታዎች በሙሉ ከሜዳው ውጪ በመጫወቱ ምክንያት የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎችን ጠንካራ ጫና በመቋቋም እና በመመከት ነበር ሲጫወት የነበረው። አሁን ግን ከረጅም ጊዜያት በኋላ ወደ ራሱ ሀገር ተመልሶ በርካታ ደጋፊ ባለው የባህር ዳር ስታዲየም በገዛ ደጋፊዎቹ ፊት መጫወት መቻሉ ለቡድኑ ትልቅ የስነ-ልቦና የበላይነት፣ ስንቅ እና ከፍተኛ ሞራል እንጂ በምንም ዓይነት መልኩ እንደ ጫና የሚቆጠር አለመሆኑን ገልጻል። የቡድኑ አባላትም የደጋፊውን መገኘት በዚሁ አዎንታዊ አቅጣጫ እንደሚመለከቱት አረጋግጧል።”
“በተጨማሪም በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ከሱዳን ጋር በነበረው ፍልሚያ ላይ በቡድኑ ዘንድ የታዩትን ጥቃቅን የታክቲክ እና የትኩረት ክፍተቶች በተመለከተ፤ ቡድኑ በስልጠናው ወቅት በእነዚህ ድክመቶች ላይ አትኩሮ በመስራት ሙሉ በሙሉ ማረሙን ተናግሯል። በመሆኑም ነገ በባህር ዳር ስታዲየም ከሴኔጋል ጋር በሚደረገው ጨዋታ ሙሉ ትኩረታቸውን ሰጥተው የነበሩባቸውን ድክመቶች ሸፍነው እና በላቀ የማሸነፍ ስሜት ብቻ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልጻል።”

