ከሸገር ከተማ ጋር ቆይታ የነበረው አማካይ ማረፊያው ጋሞ ጨንቻ ሆኗል

በአሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ መሪነት ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ አድገው በ2019 የውድድር ዓመት በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ሊጉ ያደጉት ጋሞ ጨንቻዎች ወደ ዝውውሩ በመግባት አዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እና ነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። ክለቡ ስብስቡን ለማጠናከር አሁን ደግሞ አቤኔዘር ህዝቄልን አስፈርሟል።
ከኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን የተገኘው አቤኔዜር ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሸገር ከተማ ጋር ቆይታ የነበረው ሲሆን ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ከሸገር ከተማ በስምምነት በመለያየት ወደ አዲስ አዳጊዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

