ሁለት ተጫዋቾች ልምምድ አቋርጠዋል

ሁለት ተጫዋቾች ልምምድ አቋርጠዋል

ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን እየሰራ ባለው የዋልያዎቹ ስብስብ ሁለት ተጫዋቾች ልምምድ አቋርጠዋል

በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን ወደ ሞሮኮ ተጉዞ በድል በተመለሰው ብሔራዊ ቡድናችን በዚህ ሰዓት በድሬደዋ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን እየሰራ ይገኛል።

ሆኖም አንበሉ ያሬድ ባዬ እና በመጀመሪያው ጨዋታ ቀዳሚዋን ግብ ያስቆጠረው ከንዓን ማርክነህ በልምምድ ወቅት ጉዳት አጋጥሟቸው ልምምድ አቋርጠው መውጣታቸውን መመልከት ችለናል። ከንዓን ከአየር መቀያየር ጋር ተያይዞ የአተነፋፈስ ችግር ያጋጠመው ሲሆን ህመሙ ይሄን ያህል ያልከፋ በመሆኑ ለነገው ጨዋታ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

አንበሉ ያሬድ ባዬ ግን ቡድኑ ለሁለት ተከፍሎ ባደረገው ጨዋታ እግሩ አካባቢ ግጭት የገጠመው ሲሆን ከባድ የሚመልስ ጉዳት ሳያጋጥመው እንዳልቀረና ምን አልባትም ለነገ ጨዋታ የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ እንደሆነ ታውቋል።