በዘንድሮ የውድድር ዓመት በባቱ ከተማ ያሳለፈው ግብ ጠባቂ ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሊጉ ተመልሷል

በአሠልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 27 ጨዋታዎችን አከናውነው በ38 ነጥቦች 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸው ይታወቃል። ቡድኑ የሚሳተፍበት ሊግ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ቢዘጋም በነፃ ዝውውር መሳይ አያኖን በአንድ አመት ውል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።
የግብ ዘቡ መሳይ አያኖ ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና ወልቂጤ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን በዘንድሮ የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ባቱ ከተማ ቆይታን አድርጓል። ተጫዋቹም ከሁለት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰበትን ዝውውር በዛሬው ዕለት አከናውኗል።

