ነገሌ አርሲ ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾቹን አቆይቷል

ነገሌ አርሲ ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾቹን አቆይቷል

የአሰልጣኝ ቱሉ ደስታን ውል ያራዘመው ነገሌ አርሲ የሦስቱን ቁልፍ ተጫዋቾቹ ውል ማራዘሙን ሰምተናል።

ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ባደጉበት ዓመት እጅግ አስገራሚ የውድድር ዓመት ያሳለፉት ነገሌ አርሲዎች የሦስት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘማቸውን አሁን አመሻሽ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እነርሱም ተከላካዩ ርኆቦት ስላሎ፣ አማካዩ አለኝታ ማርቆስ እና አምበሉ ዳዊት ተፈራ መሆናቸውን አውቀናል። ቡድኑ ዘንድሮ ላሳየው አስደናቂ አቋም የሦስቱ ተጫዋቾች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ከግምት ያስገቡት የክለቡ የበላይ ኃላፊዎች በቆይታቸው ዙርያ ያደረጉት ድርድር ከስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው ለተጨማሪ ዓመት ቡድኑን ለማገልገል የተስማሙት።