ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል።

ቀደም ብለው ወደ ተፎካካሪነት ያሸጋገራቸውን አሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ያራዘሙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ሰባት ተጫዋቾች ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል። አጥቂዎቹ ታሪክ ጴጥሮስ እና ቤተልሔም መንተሎ ፤ አማካዮቹ ሲሣይ ገብረዋህድ ፣ ሚልዮን ጋይም እና ሂሩት ተስፋዬ ፤ ግብ ጠባቂዋ አበባየሁ ጣሰው እና የመስመር ተጫዋቿ መሠረት ወርቅነህ በሁለት ዓመት ውል በአዲሱ የውድድር ዓመት ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ በዝግጅት ላይ ወደ ሚገኘው ኤሌክትሪክ ለመቀላቀል ፊርማቸውን ያኖሩ ተጫዋቾች ናቸው።

