ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ኤሌክትሪክ የአሰልጣኙን ውል አድሷል

ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ | ኤሌክትሪክ የአሰልጣኙን ውል አድሷል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ከመለሰውን አሰልጣኝ ጋር ለመቀጠል ተስማምቷል።

ከአንድ ዓመት በፊት ልደታ ክ/ከተማን ለቆ ወደ ኤሌክትሪክ ያመራውና እስከመጨረሻው ሳምንት ድረስ ለዋንጫ ተፎካክሮ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ ከቡድኑ ጋር ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ጋር በረዳትነት ያገለገለው ኤርሚያስ ከባንክ ቤት ወጥቶ አሁን ወዳለበት ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቶ ከአሰልጣኝ መሰረት ማኔ ጋር በረዳትነት መሥራቱ የሚታወስ ሲሆን ከዛ በመቀጠል በልደታ ክፍለከተማ ጥሩ ጊዜ አሳልፎ ላለፈው አንድ ዓመት ደግሞ በኤሌክትሪክ ቆይታ አድርጎ ቡድኑን ወደ ዋንጫ ፉክክሩ መመለስ ችሏል።