ያሬድ ካሳዬ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

ያሬድ ካሳዬ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

የግራ መስመር ተከላካዩ ማረፍያ ታውቋል ታወቋል

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በዋና አሰልጣኝነት የሾመው መቻል ዛሬ ወደ ዝውውሩ በመግባት በብዙ ክለቦች ሲፈለግ የቆየውን የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ ካሳዬን የመጀመርያ ፈራሚው አድርጓል።

በቅርብ ዓመታት ወዲህ ከታዩ ባለ ተሰጦ የግራ የመስመር ተከላካዮች አንዱ የሆነው ያሬድ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡደን ድረስ በኢትዮጵያ መድን በመጫወት የፕሪምየር ሊጉም ዋንጫም ያሳካ ሲሆን ከክለብ እግር ኳስ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ማገልገሉ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ከአሳዳጊ ክለቡ ኢትዮጵያ መድን የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ መቻል ማቅናቱ እርግጥ ሆኗል። ተጫዋቹ በአንድ ወቅት ተቀይሮ ሲወጣ ያልተገባ ባህሪ ማሳየቱን ተከትሎ መላውን የኢትዮጵያ መድን የቡድን አባላት እና የስፖርት ቤተሰቡን በይፋ ይቅርታ መጠየቁ ይታወሳል።