የመርሐ ግበር ማሻሻያና የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የማያገኙ የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች

የመርሐ ግበር ማሻሻያና የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የማያገኙ የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች

ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቅርቡ የመርሐ-ግብር ማሻሻያ ይደረግበታል በተጨማሪም በኦቤኤን የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን የማያገኙ ጨዋታዎች እንዳሉም ታውቋል

ለዋንጫ እና ላለመውረድ የሚደረገው ትንቅንቅ አጓጊነቱ ከፍ ብሎ እየተካሄደ የሚገኘው የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ የ32ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተከናውኖ ተገባዷል። ከሁለት ቀን ዕረፍት በኋላ በሚቀጥለው የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አስቀድሞ በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት የሚከወኑ ሲሆን ሆኖም ሊጉ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ምክንያት ከዕረፍት ሲመለስ የመርሐግብር መሻሻያ እና የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማይኖር ታውቋል።

በተለይ ኦቤኤን 33ኛው እና 34ኛው ሳምንታት የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን እንደማይሰጥ ሲታወቅ ከ35ኛው ሳምንት ጀምሮ ማስተላለፍ እንደሚጀምር አውቀናል። በምትኩ አክሲዮን ማህበሩ በራሱ አማራጭ በቀጥታ እንደሚያስተላለፈው ይጠበቃል። ጨዋታዋቹ ከአክስዮን ማሕበሩ የቀጥታ ስርጭት በተጨማሪ ‘ሪከርድ’ እንደሚደረጉም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ ወደ ፊት በሚገለፅ ቀናት የመርሐግብሩ ማሻሻያ ይፋ እንደሚሆን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።