ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ እግርኳስ የራሷን አሻራ እያሳረፈች የምትገኝ ዕንስት ባለሙያ የክለብ ሥራ አሰኪያጅ ሆናለች።

ለ2019 ዓ.ም በአዲስ አደረጃጀት እና መዋቅር እራሱን ለማጠናከር ከወዲሁ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ የሚገኘው አዳማ ከተማ አሁን ደግሞ አዲስ ዕንስት ሥራ አስኪያጅ መሾሙ ታውቋል።
አዳማ ከተማን በሥራ አስኪያጅነት እንድትመራ የተሾመችው ወ/ሮ ምህረት ጉታ ስትሆን ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቡድን መሪ በመሆን ስታገለግል እና በፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የውድድር ባለሙያ በመሆን በብቃት ስትመራ የቆየች ሲሆን በቅርቡ የሸገር ከተማ የሴቶች ቡድን ላይ በተለያዮ ዘርፎች ስታገለግል ከቆየች በኋላ ደግሞ አሁን የአዳማ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ሆናለች።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሲዳማ ቡና ጋር ስኬታማ የአመራርነት ሚናዋን እየተወጣች ካለችው ሴት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ከንዓን በለጠ በመቀጠል ወ/ሮ ምህረት ሁለተኛዋ ሴት ሥራ አስኪያጅ ሆናለች።

