ትናንሾቹ ሉሲዎች የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ትናንሾቹ ሉሲዎች የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

በአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ እንደሆነ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ከዛምቢያ ጋር ለሚያደርጋቸው ወሳኝ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ለዝግጅት እንዲረዳው ከዩጋንዳ ጋር ሐሙስ ሰኔ 4 የወዳጅነት ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃም በአሁኑ ሰዓት የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ከኢንቴቤ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ እየመጣ ይገኛል።