በቅርቡ ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ያደረጉት ስምምነት የተቋረጠባቸው ሀድያ ሆሳዕናዎች ሌላ አሰልጣኝ ማግኘታቸው ታውቋል።
በአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ ጋር የነበራቸው ቆይታ በመጠናቀቁ ወንበሩን በሌላ አሰልጣኝ ለመተካት ሲንቀሳቀሱ የቆዩት የሀድያ ሆሳዕና አመራሮች ተሳክቶላቸው ባለፈው ሳምንት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ለመሾም ከስምምነት ደርሰው ነበር።

ሆኖም ስምምነቱ በየትኛው ወገን እንደተቋረጠ ባይታወቅም አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ወደ አዳማ ከተማ ማቅናታቸው ከተሰማ ወዲህ ነብሮቹ ሌላ አሰልጣኝ ፍለጋ ያደረጉት ጥረት ተሳክሎ አሰልጣኝ ሳምሶም አየለን በሁለት ዓመት ውል መሾማቸው ታወቋል። ይህንን ዘገባ ባጠባከርንበት ባለንበት ሰዓትም ሁለቱ አካላት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ውሉን ለማፀደቅ እንደገቡ አውቀናል።
አሰልጣኝ ሳምሶም በቅረቡ በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በድሬደዋ ከተማ፣ በስሑል ሽሬ እና በኢትዮ ኤሌክትሪክ ማሰልጠናቸው ይታወቃል።

