የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር 9ኛውን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በቅርብ ያካሄዳል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በክለቦች ክፍያ አስተዳደር መመሪያ ዙሪያ ለመወያየት የዘጠነኛውን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ አስተላለፈ። ይህ ስብሰባ በ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፉ 18ቱም ክለቦች የተላለፈ ሲሆን በሚመጣው ሐሙስ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በዚህ አስፈላጊ ጉባኤ ላይ የየክለቦቹ ፕሬዚዳንቶች እና ሥራ አስኪያጆች እንዲገኙ የሊጉ አክሲዮን ማህበር ያሳሰበ ሲሆን ስብሰባው የሚካሄድበት ሆቴል በቅርብ ቀናት ውስጥ ተለይቶ ይፋ እንደሚደረግ ታውቋል።

