ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወደ ፌይኖርድ አመራ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወደ ፌይኖርድ አመራ

ተስፈኛው ትውልደ ኢትዮጵያዊው የመስመር ተጫዋች ወደ ፌይኖርድ አምርቷል

በውድድር ዓመቱ 17 ግቦችን በማስቆጠር ግሩም ዓመት ያሳለፈው የ15 ዓመት ተስፈኛ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሳሚል ኮሮማ እስከ 2029 በሚቆይ ውል ፌይኖርድን ተቀላቅሏል።

ስሙ የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ ጨምሮ ከበርከት ያሉ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው ይህ ተስፈኛ ተጫዋች በአዲሱ የውድድር ዓመት የፌይኖርድ 17 ዓመት በታች ቡድንን የሚቀላቀል ሲሆን ከፌርማ ስነ ስርዓቱ በኋላም “ለፌይኖርድ መጫወት ህልሜ ነበር ፤ ጠንክሬ እሰራለሁ ከአሰልጣኞቼ እና ከቡድን አጋሮቼም እማራለሁ እንዲሁም የተሻለ ተጫዋች ለመሆን ያለኝን ሁሉ እሰጣለሁ” ብሏል።

ሳሚል ኮሮማ ከኢትዮጵያዊት እናት እና ከናይጄርያዊ አባት በኔዘርላንድስ የተወለደና በሚጫወትበት የዕድሜ እርከን ውስጥ ድንቅ ብቃቱን ያሳየ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ታዳጊ ሲሆን ወደ Emmen አካዳሚ ከመቀላቀሉ በፊት በ ‘vv Bargeres እና አሁን መንትያ ወንድሙ በሚጫወትበት ‘vv Drenthina’ የታዳጊ ክለቦች ቆይታ ማድረግ ችሏል።

ከኢትዮጵያዊ አባት እና ከኤልሳልቫዶራዊት እናት የተገኘውና በአሁኑ ወቅት በኢንግሊዝ ቻምፕዮንሺፑ ‘QPR’ በመጫወት ላይ የሚገኘው የአስራ ዘጠኝ ዓመቱ ይስሀቅ ሙልጌታም ከዚህ ቀደም በዚህ የኔዘርላንዱ ክለብ የወጣቶች ቡድን ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል።