“ታሪክ ለመሥራት ዝግጁ ናቸው።” አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ

“ታሪክ ለመሥራት ዝግጁ ናቸው።” አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ


👉 “ለመለወጥ ራሳቸውን ዝግጁ ያደረጉ ሰሚ ትውልድ ናቸው።”

👉 “በጥንቃቄ ተጫውተን የተሻለ ነገር ሠርተን ለመምጣት እናስባለን።”

👉 “ያሉትን ልጆች አንድነት ጠብቀን የዓለም ዋንጫ ለመግባት እንጥራለን።”

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ ዙርያ አሰልጣኝ ራውዳ አሊ ምን አሉ?

ወደ ዓለም ዋንጫው ለመሻገር የመቶ ሰማንያ ደቂቃ ጊዜ የቀረው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ከዛምቢያ ጋር ላለበት ጨዋታ ያደረገው ዝግጅት እና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን አስመልክቶ ዛሬ  የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ራውዳ አሊ እና አንበሏ ምህረት ወሰን በጋራ በመሆን ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ሶከር ኢትዮጵያም በስፍራው በመገኘት አሰልጣኝ  ራውዳ  የተናገሯቸውን ዋና ሀሳቦች እንዲህ አቅርበነዋል።

“ተጋጣሚያችን በጣም ጠንካራ እና ፈጣኖች እንደሆኑ እናምናለን እኛም ጠንካራ ቡድን እንደሆንን እምነቱ አለን እነርሱን በሚመጥን መልኩ ከዩጋንዳ ጋር ጨምሮ ከወንዶች ቡድን እና ከንግድ ባንክ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርገናል በዚህም ቡድናችን ያለውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን በበቂ ሁኔታ ለማየት ሞክረናል” ያሉት አሰልጣኝ ራውዳ “ከዚህ ቀደም አንድ ብሔራዊ ቡድን ነው ወደ ዓለም ዋንጫ የተሻገረው አሁን ይህን አንቺ ለማሳካት ምን ታስቢያለሽ ተብሎ ለተነሳላት ጥያቄ ስትመልስ”

“በተለያየ ጊዜ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ምዕራፍ ደርሰን ባለመሳካቱ ቁጭት አለብን በወንዶች ወጣት ቡድን የዓለም ዋንጫ አልፈናል። እኛ ደግሞ የራሳችንን ታሪክ ለመሥራት፣ በሴቶች እግርኳስ ትኩረት እንዲደረግ በማሰብ በአለን አቅም ያለውን አንድነት በመጠበቅ ውጤታማ ለመሆን የምንችለውን ጥረት እናደርጋለን” ብለዋል። አክለውም አሁን ያለው የቡድን ስብስብ ራሳቸውን ዝግጁ ያደረጉ ጆሯቸውን የሚሰጡ ሰሚ ትውልድ ናቸው። ብለዋል።