“ጠንካራ ሆነን ነው እዚህ ደረጃ የደረስነው” ምሕረት ወሰኑ

“ጠንካራ ሆነን ነው እዚህ ደረጃ የደረስነው” ምሕረት ወሰኑ

👉” የኢትዮጵያ ሕዘብ ከጎናችን እንዲሆን እና እንዲደግፈን…

👉 “የዓለም ዋንጫ ማለፍ ቀላል አይደለም ድጋፋችሁ አይለየን”

👉 “ዛምቢያ በጣም ጠንካራ ቡድን እንደሆነ እናውቃለን እኛም ጠንካራ ሆነን ነው እዚህ ደረጃ የደረስነው።”

የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ቡድነ አንበል ምሕረት ወሰኑ በወሳኙ ጨዋታ ዙሪያ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥታለች።

ነገ ወደ ዛምቢያ ከማቅናቱ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በጉዞው እና ዝግጅቱ ዙርያ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ራውዳ አሊ የሰጠችውን ማብራሪያ ከደቂቃዎች በፊት በሰፊው ማቅረባችን ይታወቃል። በመቀጠል የቡድኑ ዋና አንበል ምሕረት ወሰኑ ስለ ቡድኑ ዝግጅት እና በቀሪው የመቶ ሰማንያ ደቂቃ ፍልሚያ ከቡድን አጋሮቿ ጋር ሊያደርጉት ያሰቡትን ሀሳብ እንዲህ ተናግራለች።

“ወደ ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻው ዙር ጨዋታዎች ደርሰናል ቡድናችን ያለበት ሁኔታ በጣም አሪፍ እና ታሪክ ለመሥራት ዝግጁ ነን። በፍላጎት ያለን ዝግጅት ጥሩ የሚባል እና የቡድን መንፈሳችን በጣም ጥሩ ነው። ዛምቢያ በጣም ጠንካራ ቡድን እንደሆነ እናውቃለን እኛም ጠንካራ ሆነን ነው እዚህ ደረጃ የደረስነው።”

“ማንንም ቡድን አክብደንም አሳንሰንም አናይም
በተዘጋጀንበት ልክ ማድረግ ያለብን ለማድረግ ዝግጁ ነን በድል እንመለሳለን።” ካለች በኋላ

“የመጀመርያ ጨዋታ ከሀገር ውጭ እንደምንጫወት እናውቃለን ጫና አለ በጣም ብዙ ደጋፊ አላቸው። አዲስ አበባ በሚኖረው የመልስ ጨዋታም የኢትዮጵያ ህዘብ ከጎናችን እንዲሆን እንዲደግፈን የዓለም ዋንጫ ማለፍ ቀላል አይደለም ድጋፋችሁ አይለየን” በማለት ተናግራለች።