👉 “ተጫዋቾቻችን ልጆች ከመሆናቸው አንፃር የምንፈልገው እንቅስቃሴ ተግባራዊ አላደረግንም”
👉 “ከፍተኛ ጉጉት ስለነበር ውጤቱ ለዓለም ዋንጫ ሊያሳልፈን አልቻለም”
👉 “አሰልጣኝ ነኝ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ”
👉 “ተጋጣሚያችን ካንድም ሁለቴ ለዓለም ዋንጫ ያለፈ ትልቅ ቡድን ነው”

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከዛምቢያ አቻቸው ጋር ዛሬ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ባድረጉት ጨዋታ በድምር ውጤት 2ለ3 ተሸንፎ ለዓለም ዋንጫ ሳያልፍ ከቀረ በኋላ ዋና አሰልጣኝ ራውዳ አሊ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን አስተያየት በሶከር ኢትዮጵያ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።
ጨዋታው እንዴት ነበር?
በጨዋታው ጫና ውስጥ ገብተን ነበር ልጆቻችን ልጆች ከመሆናቸው አንፃር ምንፈልገውን እንቅስቃሴ ተግባራዊ አላደርግንም ግን ሚጠበቀው ከፍተኛ መነሳሳት እና ለዓለም ዋንጫ ሀገራችንን ለማሳለፍ ታሪክ ለመስራት ጉግት ስለነበራቸው ታዳጊ እስከሆኑ ድረስ ትንሽ ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነበረና እሱን ለመቆጠጣር ሙከራ አድርገን ነበር። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ በአንድ ደቂቃ ነበር የገባበን እሱን ለመቆጣጠር ታክቲካሊ እና የፎርሜሽን ለውጦችን አድርገን ነበር፤ የመሃል ተጫዋቾችን አብዝተን ወደፊት ለማጥቃት ሙከራ አድርገናል አንድ ጎል እንድናገኝ አድርጎናል። ጉጉት ስለነበር ውጤቱ እኛን ለዓለም ዋንጫ ሊያሳልፈን አልቻለም።
የቅያሪዎቹ መዘግየት ምክንያቱ ምን ነበር?
ቡድኑን የሰራነው ለአርባአምስት ብቻ አይደለም። ልጆቹን በትዕግሥት ማድረግ አለብን። መሃል ላይ ትንሽ እንቅስቃሴው ሂደቱ ረጃጅም ኳሶችን እንፈልግ ነበር ወደፊት ማጥቃት ስለምንፈልግ እዛ ጋር ኮፍተት ነበር ያየነው እረፍት ላይ አንድ ተጫዋች ቀይረናል። እነዚህ ልጆች ብዙ ጊዜ አብረው ስለቆዩ አዳዲስ የነበሩት አጥቂ ቦታ ላይ የነበሩ ልጆች እምነት ስለነበረ በእነሱ ላይ አጥቂ ላይ ትንሽ ዘገየት ብለናል። ግን ልዩነት ፈጣሪ ተጫዋች እንደሆነችም አይተናል በዛውም።
የዛምቢያ አሰልጣኝ የኢትዮጵያን ጥሩ ተጫዋቾችን ማርክ በማድረግ ነበር ትልቁ ስትራቴጂያችን ብላ እሱንም ምህረትን እንዳትጫወት አድርገው አይተናል፤ በሁለተኛው አጋማሽ እሱን ነገር የማስተካከል ነገር ነበር ወይ ?
ሁሉም ጥሩ ተጫዋቾች ናቸው። ያው ጎሎችን ታስቆጥራለች ምህረት አየለ ግን ባለው ነገር ወደ ውስጥ እየገባች እራሷን ነፃ እያደረገች እንዲትጫወት ከአጋማሱ በኋላ ሰርተን ነበር፣ ጎሉ ገና ከጅምሩ ስለገባብን እንቅስቃሴው ወደ ምፈልገው መንገድ አልሄደም እንደገና ደግሞ በአንድ ለአንድ ግንኙነት ብልጫ ነበራቸውና ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ያረጓት ነበረና ሌሎችም እኛ የምናስባቸው ልጆች ነበሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገቡልናል ብለን የምናስባቸው በምንፈልገው ልክ አልተንቀሳቀሱም። ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር ማድረግ ስላልቻሉ ቁጭት ውስጥ ነው ያሉት። እራሷን ነፃ አድርጋ እንዲትጫወት ወደ መሃል እየገባች እንዲትጫወት ነበር ያደረግነው ግን ቻርጅ ስለበዛባት ፍራትም ነበር።
ለዓለም ዋንጫ ስላላለፍን ሀላፊነቱን ይወስዳሉ ወይስ ምንድነው የሚያቀርቡት ምክንያት ?
አሰልጣኝ ነኝ ሀላፊነቱን ወስዳለሁ።
ግብ እስኪቆጠር ድረስ በተደጋጋሚ እነሱ ሲያጠቁ የነበሩት እነሱ ነበሩና ስትራቴጂ ነው ወይስ ከተጋጣሚው አንፃር ተገዳቹ ያደረጋቹት ነገር ነው?
ተጋጣሚያችን ካንድም ሁለቴ ለዋንጫ ያለፈ ትልቅ ቡድን ነው። ሀገራቸው ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ እኛም አድርገናል እነሱም የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገዋል። ሌላ ተጨማሪ ጎል እንዳይቆጠርብን እና እኛ የምናገኘውን አጋጣሚ ወደፊት ሄደን ጎሎችን ለማስቆጠር ነበር የኛ ስትራቴጂ። ጎሎች ከገቡብን ተጨማሪ ጎሎች ነው የምናገባው እና መጀመሪያ የተከላካይ መስመራችንን ዘግተን የተሻለ ኳሶችን ወደፊት ለማድረግ ነበር መስርተን የተሻለ ነገር ለማድረግ ነበር። ፕሬሲንጋቸው ከፍተኛ ነበርና የምንፈለገውን እንቅስቃሴ እንዳናደርግ ልጆች ቶሎ ወደጨዋታ ለመግባት ትንሽ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበሩ። ፍላጎቻቸው ከፍ ያለ ነበር አሸንፈው ከዛ በኋላ ያለውን ደስታ ነበር ጉጉታቸው እና በተቻለ አቅም በሀገራቸው ያደረግነውን ነገር ብናደርግ ውጤቱ ይሄ አይሆንም ነበር።

