አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የሽልማት መርሐግብሩ ላይ ምን ተናገሩ?

አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የሽልማት መርሐግብሩ ላይ ምን ተናገሩ?

👉 “ቻምፒዮን የምትሆኑ ክለቦች ሀገራችንን ሊያስከብር የሚችል ቡድን ሠርታችሁ ዐሳዩን።” አቶ ኢሳይያስ ጂራ

👉 “እግርኳሳችን ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ ራሳችንን አሳምነን ከዛ መጀመር አለብን።” አቶ ኢሳይያስ ጂራ

👉 “130 ሚሊዮን ህዝብ ይዘን ሰበታን ከማታክል ሀገር ጋር ነው ማጣሪያ ምናደርገው።” አቶ ኢሳይያስ ጂራ

👉 “በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

👉 “ከ2013-2018 በነበረው የውድድር ዘመን ከሱፐር ስፖርት ያገኘነውን 1,260,000,000 ብር ለክለቦች አከፋፍለናል።” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቦች የሽልማት መርሐግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቀደ ማሞ ዘንድሮ በሁለት ሜዳዎች በተመሳሳይ ሰዓት ጨዋታዎች ሲተላለፉ ነበር  ከዚህ ልምድ በመነሳት ጨዋታዎቹን ወደ አራት እና አምስት ሜዳዎች ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነው ሥርጭቱም ይቀጥላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።” ያሉ ሲሆን በደንቡ መሠረት አራት ቡድኖች ከሊጉ መውረዳቸውን እና በቀጣዩ የውድድር ዘመንም በተመሳሳይ አራት ቡድኖች እንደሚወርዱ አሳስበዋል።

ከእሳቸው በመቀጠል ሰፋ ያለ ገለጻ ያደረጉት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በበኩላቸው “እግርኳሳችን ከኢትዮጵያ ውጪ የማይታይበት ጊዜ ደርሶ ነበር። የታንዛኒያውን አዛምን ሳይ እቀና ነበር በዚህም Obn’ን አመሠግናለሁ።” ካሉ በኋላ

“ማስገንዘብ ምፈልገው እግርኳሳችን ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ ራሳችንን አሳምነን ከዛ መጀመር አለብን። ቻምፒዮን ሁሌ እንሸልማለን ስንቶቹ ናቸው ከመጀመሪያው ዙር ያለፉ? ታንዛኒያ በቻምፒዮንስ ሊጉ ሁለት ኮታ አላቸው ተሳታፊዎች ወደፊት ስትሄዱ ኮታችን ይጨምራል።ቻምፒዮን የምትሆኑ ክለቦች ሀገራችንን ሊያስከብር የሚችል ቡድን ሠርታችሁ ዐሳዩን። ስንቶቻችን ነን የወጣት ልማት ላይ ምንሠራው? እኛ በ4 ዓመት ውስጥ በፓይለት ፕሮጀክት ቡድናችን ለአፍሪካ ዋንጫ አሳልፈናል። ተስፋ ቢኖርም አለመሥራታችን ይቆጫል። ክለቦች የራሳችሁን ሌጋሲ ገንቡ ስንት ተጫዋቾች አወጣን ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ብሔራዊ ቡድናችንን ሊቆጨን ይገባል። እነ ሶማሊያ እና ጂቡቲ ውስጥ ገብተናል። 130 ሚሊዮን ህዝብ ይዘን ሰበታን ከማታክል ሀገር ጋር ነው ማጣሪያ ምናደርገው። አንዱ ጠባቂ አንዱ ተጠባቂ መሆን የለበትም። ዓለም የሠራውን ሥራ ከሠራን ማናድግበት ምክንያት የለም። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛምቢያ ላይ ተሸንፎ መጥቷል ለዓለም ዋንጫው ለማለፉ 90 ደቂቃ የቀረ ሲሆን በሜዳችን ውጤቱን እንቀለብሳለን ደጋፊዎች ሜዳ ላይ ተገኙ! ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ።” ሲሉ ኮስተር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል።