የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው አሰልጣኝ ውሉን ለማራዘም ተስማማ

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው አሰልጣኝ ውሉን ለማራዘም ተስማማ

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ከቢጫዎቹ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ደርሰዋል

በቅርቡ ሲዳማ ቡናን ሁለት ለባዶ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ዋንጫን በማንሳት በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ውድድር ተሳትፎ ያረጋገጡት ወልዋሎዎች የዋና አሰልጣኛቸው ግርማ ታደሰ ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።

ለቀናት ካደረጉት ውይይት በኋላ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ውላቸውን በማራዘም ከወልዋሎ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ግርማ ፈታኝ በነበረው የመጀመሪያው ዓመት የቡድኑ ቆይታቸው በፕሪምየር ሊጉ የሚያተርፋቸውን ውጤት አስመዝግበው የኢትዮጵያን ዋንጫ ማሳካታቸውን ይታወሳል። በሦስት አጋጣሚዎች ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ ማሳደግ የቻሉት አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም ስልጤ ወራቤ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ ፣ ደቡብ ፖሊስ እና ሀድያ ሆሳዕና ማሰልጠናቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በቢጫዎቹ ቤት ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ከስምምነት ደርሰዋል።