ዐፄዎቹ የአሰልጣኛቸውን ውል ለማራዘም ተቃርበዋል

ዐፄዎቹ የአሰልጣኛቸውን ውል ለማራዘም ተቃርበዋል

ፋሲል ከነማ ያለፉትን ወራት ቡድኑን የመሩትን አሰልጣኝ ለማቆየት የክለቡ ቦርድ መወሰኑን አውቀናል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌን ከፋሲል ከነማ ጋር በስምምነት ተለያይተው ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መሄዳቸውን ተከትለው ከጊዜያዊ ረዳት አሰልጣኞች በኋላ ቡድኑን የተረከቡት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ቡድኑን እየመሩ በሃምሳ አምስት ነጥብ አራተኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ አስችለውታል።

አሰልጣኙ ቡድኑን በተሻለ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ማድረጋቸውን የተገነዘበው የክለቡ ቦርድ ዛሬ ከአሰልጣኝ ዘማርያም ጋር ድርድር የተቀመጠ መሆኑ ሲታወቅ በሁለቱም መካከል ያለው ንግግር በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ ከቡድኑ ጋር ለሁለት ዓመት እንዲቆዩ መወሰኑን አውቀናል። በቀጣዮቹ ቀናትም ፊርማቸውን በይፋ ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ዘማርያም ከዚህ ቀደም በባሕር ዳር ፣ በፋሲል ከነማ ፣ ወልዲያ ፣ አዳማ ከተማ፣ ወልዋሎ ዓ/ዩ ፣ ጅማ አባ ጅፋር፣ ድሬዲዋ ከተማ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ሻሸመኔ ከተማን ማሰልጠናቸው ይታወቃል።