ሀብታሙ ተከስተ ወደ ቡናማዎቹ አምርቷል

ሀብታሙ ተከስተ ወደ ቡናማዎቹ አምርቷል

በዝውውሩ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች አራተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

በአዲስ አሰልጣኝ እና በአዲስ የቡድን ግንባታ ለቀጣይ የውድድር ዓመት እራሳቸውን ለመጠናከር እንቅስቃሴ በማድረግ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች አስቀድመው የግብ ዘቡን አቡበከር ኑራ ፣ በረከት ወልደ ዩሐንስ እና አብዱልሰላም የሱፍን ለማስፈረም የተስማሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ሀብታሙ ተከስተን የግላቸው ለማድረግ መስማማታቸው ታውቋል።

በዳሽን ቢራ የእግርኳስ ህይወቱ የጀመረው ሀብታሙ በመቀጠል በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ፣ በመቐለ 70 እንድርታ እንዲሁም ያለፉተን ሰባት ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት ቆይታ በማድረግ የሊጉን ዋንጫ ማሳካቱ ይታወቃል። ሀብታሙ ረጅም ወራቶች በእግርኳስ ህይወቱ እጅግ ፈታኝ የሚባል ህመም አጋጥሞት ቢሰነብትም ዳግም ወደ ሊጉ በመመለስ ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱን ሲታወስ አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቷል።