የጦና ንቦቹ ቁመታም ሴኔጋላዊ ተከላካይ አስፈርመዋል

የጦና ንቦቹ ቁመታም ሴኔጋላዊ ተከላካይ አስፈርመዋል

ሴኔጋላዊው የመሃል ተከላካይ ወላይታ ድቻን መቀላቀሉን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ቡደኑ ከተረከቡበት ጊዜ ወዲህ ጥሩ መሻሻል ያሳዩት እና ለቀጣይ የውድድር ዓመት ራሳቸውን በማጠናከር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት ወላይታ ድቻዎች በትናንትናው ዕለት በረከት ወልዴን ሲያስፈርሙ ዛሬ ደግሞ ሴኔጋላዊ የመሃል ተከላካይ ለማስፈረም መስማማታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ቡድኑን የሚቀላቀለው ተጫዋች አዳማ ዋዴ ሲሆን ይህ 1.94 ሜትር ቁመት ያለው ተጫዋቹ በትልቅ ሊግ ደረጃ በሀገሩ ክለብ ሳክሬ ጅማሮውን አድርጎ ለቱርኩ ኡምራኒየስፖር እና በጆርጂያው ሎኮሞቲቭ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ሀገሩ ሴኔጋል ተመልሶ ለጉይዲያዋየ ፣ ለቀድሞ ክለቡ ሳክሬ እንዲሁም ለኤኤስሲ ጃራፍ የተጫወተ ሲሆን ከሦስት ሳምንት በፊት ለኮትዲቫሩ ያሞውሱክሮ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ለጦና ንቦቹ ለመጫወት ተስማምቷል።

በወላይታ ድቻ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ክለቡን ለማገልገል በግማሽ የተቀላቀሉት ግብ ጠባቂው ካዲሚ ድያዬ፣ አማካይ ኦኮጄፓ ኣውግስቲን እና የመስመር አጥቂው ሳሊፉ ኢብራሂም ጥሩ ጊዜ ማሳለፋቸው ይታወሳል።