ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ምርጥ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ተጫዋች ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለማምራት መቃረቡን ሶከር ኢትዮጵጵያ አረጋግጣለች

የግራ መስመሩ ተከላካዩ ያሬድ የማነ ከእናት ክለቡ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የነበረው የዓመታት ቆይታ መጠናቀቁ ይታወቃል። ተጫዋቹ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲነሳ ቢቆይም ትናንት አመሸሻ ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ አመራሮች ጋር ያደረገውን ድርድር አጠናቆ በእግርኳስ ህይወቱ ሁለተኛ የሆነውን የፈረሰኞቹ መለያ ለመልበስ ለሁለት ዓመት ለመጫወት መስማማቱን አውቀናል።
በተጠናቀቀው የውድደር ዓመት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ በሠላሳ ስድስት ጨዋታዎች ተሳትፎ 3170 ደቂቃዎች በማገልገል አንድ ጎል አስቆጥሮ ድንቅ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ተጫዋቹ በሶከር ኢትዮጵያ የዓመቱ ምርጥ አስራ አንድ ምርጫ ውስጥም መካተቱ ይታወቃል።
ፈረሰኞቹ በመቀጠል ውል የማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡደኑ የመቀላቀል ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል።

