በጣምራ የሊጉ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ወደ አንጋፋው ክለብ አቅንቷል

በጣምራ የሊጉ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ወደ አንጋፋው ክለብ አቅንቷል

ዘንድሮ በአስራ አምስት ጎሎች በጣምራ የሊጉ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀው  አጥቂ ወደ አንጋፋው ክለብ ለማምራት ተስማምቷል።

በሾኔ ከተማ መነሻውን ያደረገው እና በቤንች ማጂ ቡና ባሳየው ድንቅ ብቃት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጥቶ ስኬታማ ቆይታ ያደረገው ናትናኤል ዳንኤል አሁን መዳረሻው ፈረሰኞቹ ጋር መሆኑን አውቀናል። ለሁለት ዓመት ለቅዱስ ጊየርጊስ ለመጫወት የተስማማው ናትናኤል በዘንድሮ ዓመት አስራ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነትን ከታምራት ኢያሱ ጋር መጋራቱ ይታወቃል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ስብስቡን አጠናክሮ ለመቅረብ በሚያደርገው ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርም ሰምተናል።