የጦና ንቦቹ የመስመር አጥቂውን ለማስፈረም ተቃርበዋል

የጦና ንቦቹ የመስመር አጥቂውን ለማስፈረም ተቃርበዋል

ያለፉትን ዓመታት ከአርባምንጭ ከተማ ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂ ወደ ጦና ንቦቹ አምርቷል።

በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች ወደ ዝውውሩ በመግባት ራሳቸውን ለማጠናከር እየሰሩ ሲሆን አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂውን በፍቅር ግዛቸውን ለማስፈረም መቃረባቸውን አውቀናል።

በሲዳማ ቡና ታዳጊ ቡደን ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ወደ አርባምንጭ ከተማ ከመጣ ወዲህ ጥሩ የሚባሉ የውድድር ጊዜዎችን ሲያሳልፍ የቆየው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ በፍቅር ግዛቸው አሁን ከአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጋር አብሮ ለመስራት ማረፊያውን ወላይታ ድቻ ለማድረግ መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።