አዲስ አዳጊዎቹ ሁለት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማሙ
በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ በመግባት ሁለቱ ጋናዊያን ኮንኮኒ ሐፊዝ እና ካሌብ አማንክዋህን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸውን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሰዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማሙት ተጫዋቾች ደግሞ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በመቻል መጫወት የቻለው የመሀል ተከላካዩ ነስረዲን ሀይሉ እና ከዚህ ቀደም በለገጣፎ ለገዳዲ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ላለፉት ሁለት ዓመታት በወልዋሎ ጥሩ ቆይታ የነበረው ኪሩቤል ወንድሙ ናቸው።

