በየነ ባንጃው ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል

በየነ ባንጃው ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ቡድናቸውን ማጠናከር ገፍተውበታል።

የነፃነት ገብረመድህን ፣ ሰመረ ሀፍታይ እና የስምዖን ማሩን ውል አራዝመው እዮብ አለማየሁ ፣ በረከት ሳሙኤል ፣ ካርሎስ ዳምጠው እና ማማዱ ሴክን የግላቸው ለማድረግ ከስምምነት የደረሱት ቢጫዎቹ አሁን ደግሞ የአማካዩ በየነ ባንጃው ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሰዋል።

ውሉን ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም የተስማማው  ከአፍሮ ፅዮን ከ17 ዓመት በታች ቡድን የተገኘው በየነ ከዛ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን፣ በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት እንዲሁም ከ 20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን፣ በገላን ከተማ እንዲሁም በሀድያ ሆሳዕናና ወልዋሎ ቆይታ ማድረጉ ሲታወስ አሁን ደግሞ በቢጫዎቹ ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል።