በረከት ግዛው ወደ አዲስ ክለብ ተጉዟል

በረከት ግዛው ወደ አዲስ ክለብ ተጉዟል

ከዐፄዎቹ ጋር ድንቅ ዓመት ያሳለፈው አማካይ ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት ተቃርቧል

ከጂንካ የተገኘው እና በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በፋሲል ከነማ መለያ ራሱን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ በደንብ ማስተዋወቅ የቻለው አማካዩ በረከት ግዛው ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ የነበረው ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣይ ማረፊያው የት ሊሆን ይችላል የሚለው ተጠባቂ ሆኖ ቆይቷል።

ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ የአማካዩ ማረፊያ ነገሌ አርሲ ሊሆን መቃረቡን እና ከክለቡ ጋር ያደረገው ድርድር በስምምነት መቋጨቱ ተሰምቷል። በረከት ግዛው በ2016 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በነበረው ቆይታ በ2016 የሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረግ ችሎ ነበር።