ነብሮቹ አዲስ ተጫዋች አግኝተዋል

ነብሮቹ አዲስ ተጫዋች አግኝተዋል

በአሠልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚመራው ሀዲያ ሆሳዕና አዲስ ተጫዋች አግኝቷል።

ሳምሶን አየለን የቡድኑ አሠልጣኝ አድርጎ የሾመው ሀዲያ ሆሳዕና በዝውውሩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለት የአጥቂ አማካዩን ያሬድ ታደሰን የግሉ ማድረጉን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።
የድሬዳዋ ከተማ እና የወልቂጤ ከተማ ተጫዋች የሆነው ያሬድ ታደሰ ከወልቂጤ ተመልሶ ድሬዳዋ ከተማን ያለፉትን አራት አመታት ካገለገለ በኋላ ወደ ነብሮቹ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል።