ሐይቆቹ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ በመግባት የሁለት ተጫዋችን ውል አራዝመዋል

ውሉን ያደሰው የመጀመሪያ ተጫዋች ከታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ ላለፉት ስድስት አመታት ቡድንኑ በግብ ጠባቂነት ሲያገለግል የቆየው ምንተስኖት ጊንቦ ለሚቀጠሉት ሁለት ዓመት ከክለቡ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል።
ሌላኛው ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ብሩክ ታደለ ሲሆን ከታዳጊ ቡድን አድጎ ክለቡን ሲያገለግል የቆየው የግራ መስመር ተመላላሽ እንዲሁም የተካለካይ አማካይ ሆኖ መጫወት የሚችል ሁለገቡ ተጫዋቹ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ከክለቡ ጋር ለመቆየት መስማማቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

