ጦሩ ስድስተኛ አዲስ ፈራሚው አግኝቷል

ጦሩ ስድስተኛ አዲስ ፈራሚው አግኝቷል

በቀጣዩ የውድድር ዓመት በዋንጫ ፉክክሩ ራሱን ለማግኘት ቡድኑን እያጠናከረ የሚገኘው መቻል አማካይ አስፈርሟል።

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው መቻል ስብስቡን እያጠናከረ የሚገኝ ሲሆን ከቀናት በፊት ከፈፀማቸው ሦስት የሀገር ውስጥ ዝውውሮች በተጨማሪ ሁለት የውጪ ተጫዋቾችን ዝውውር ከሰዓታት በፊት መፈፀሙን ዘገባ ያቀረብን ሲሆን አሁን ደግሞ ሦስተኛ የውጪ ተጫዋቹን በድምሩ ስድስተኛ አዲስ ተጫዋች ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የጦሩ ስድስተኛ ተጫዋች የሆነው ሱዳናዊው ሙዳቲር ያህያ መሐመድ ዳውድ ነው። ከስድስት ዓመታት በላይ በደቡብ ሱዳኑ ክለብ ጃሙስ ያሳለፈው የ26 ዓመቱ አማካይ ሙዳቲር ያህያ ለወራት ካሰለጠኑት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ዳግም ለመስራት በአንድ ዓመት ውል ወደ መቻል የሚያደርገውን ዝውውር ፈፅሟል።